በበሁለተኛው የኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ ቂርቆ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በበሁለተኛው የኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኡራኤልና የአትላስ አካባቢ የግል ባለይዞታ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች የምትክ ቦታ ለመረከብ የሚያስችል እጣ ማውጣት መርሐ ግብር እንደቀጠለ ነው።

ተነሺዎቹ በግል ይዞታ የሚኖሩ ሲሆን ከዚህ በፊት የልማት ተነሺዎች ግልፅና ይፋዊ በሆነ መልኩ እጣ በማውጣት እየተረከቡ መሆኑ ተገልጿል።

በዛሬው እለትም የግል ባለይዞታዎች የሚነሱበትን አካባቢ መነሻ በማድረግ የምትክ ቦታ መረከብ መጀመራቸው የተገለፀ ሲሆን ነገን ጨምሮ ምትክ ቦታ የመረከቡ ስራ የሚቀጥል መሆኑም ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ በኮሪደር ልማት ከተማዋን ከማስዋብ ባሻገር የህዝቡን አኗኗር ባህል እየቀየረ ስለመሆኑ የልማት ተነሺዎች እጣ አወጣጥ አንዱ ማሳያ መሆኑን በእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

አዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.