"የቀበና ወንዝ ዳርቻ ስራችን የከተማችንን ነዋሪ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ፕሮጀክት በታቀደለት ጊዜ እና ጥራት ለማጠናቀቅ 24/7 ይሰራል"፦ አቶ ሞገስ ባልቻ
የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ፣የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ ጨምሮ የክፍለ ከተማ አመራሮችና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት በ2ኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረው ምልከታ አደረጉ።
የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ የወንዝ ዳርቻ ፕጀክቱ ሲጠናቀቅ ለከተማዋ አዲስ ገፅታን ከማላበሱ ባለፈ የቱሪስት መዳረሻነሻቷ እንዲጨምር እና ለነዋሪዎቿ ተስማሚ፣ ውብና ማራኪ ገፅታን የሚያጎናፅፍ ፕሮጀክት በመሆኑን
የ2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የቀበና ወንዝ ዳርቻ ስራችን ፕሮጀክት በታቀደለት ጊዜ እና ጥራት ለማጠናቀቅ 24/7 በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን በምልከታው ገልፀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.