19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ " ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ በታላቅ ድምቀት ተከበረ::

ኢፌዴሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንደተናገሩት ሃገራችን ብዝሃነት ካላቸዉ የአለም ሃገራት አንዷ መሆኗንና ይህንንም ከትዉልድ ትዉልድ ለማስቀጠል በዉይይትና በምክክር በመስራት የሃሳብ ልእልና ማረጋገጥ እንደሚጠበቅ ገልፀዉ ለሃገራዊ መግባባት እና ለፌደራላዊ ሃገራዊ ግንባታ ስርዓት ማደግ በጋራ መቆም አለብን ብለዋል፡፡

አክለዉም አዲስ አበባ ሁሉም ከየአቅጣጫዉ የተሰባሰቡባትና የሚኖሩባት ማሳያና አምሳያ ስትሆን ለዚህም የሁሉም አሻራ ያረፈባት፤የሁሉም ላብ የፈሰሰባት፤የሁሉም እጆች ያበጃጇት፤የወል ታሪክ የተፃፈባት ህብረብሄራዊ ትስስር ያደመቃት የልህቀት ማእከል ከተማ መሆኗን ገልጸዉ ይህም የብልፅግና ጉዞአችን እዉን አድርጎ ያስቀጠለዉ መሆኑን አዉቀን ትዉልዱ የእርስ በእርስ ትስስሩ በማስፋት ለሰላምና ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት የጀመረዉን ጉዞ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ብዘሃነትን ያቀፈች በመሆኗ የማንነት የባህል የቋንቋ የእምነት እና የተለያዩ ትዉፊቶች የሚንፀባረቁባት ብዝሃነትን ያስተናገደች ድንቅ ሃገር ነች ያሉት ከንቲባዋ ይህን ብዝሃነት በወጉ አክብሮ በእኩልነት እና በፍትሃዊነት የሚነሱ ጥያቄዎችን በአግባቡ በመመለስ እና በማረጋገጥ የኢትየጵያን አንድነት በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነትና ለፌደራላዊ ስርዓት ግንባታ ወሳኝ ሚና አለዉ ብለዋል፡፡

አክለዉም ብዝሃ ማንነታችን ከፈጣሪ የተሰጠን ፀጋዎቻችን በመሆናቸዉ እኛ ኢትዮጰያዉያን ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ የብልፅግና ጎዞአችን ለማሳካት እጅ ለእጅ ተያይዘን በማንነታችንና በብዙህነታችን ደምቀን በእኩልነት ላይ የኢትዮጵያን አንድነት በጠንካራ መሰረት ጠንካራ ህዝብና ሃገር መንግስት እየገነባን እንገኛለን ብለዋል።

ይህም በጥሩ ሁኔታ ዉጤት እየታየበት ያለ የብልፅግና ጉዞ በመሆኑ አዲስ አበባ ለዚህ ህብረብሄራዊ አንድነት ማሳያ ትልቋ የኢትዮጵያ ቤት መሆኗን ገልፀዉ በማህበራዊዉ በኢኮኖሚዉና በፖለቲካዉ በጀመርናቸዉና ባሳካናቸዉ የለዉጥ ጉዞ ትዉልዱ በመከባበብር እና በመፈቃቀር ላይ የተመሰረተ የጋራ ልማት ለጋራ ተጠቃሚነት በመስራት አላስፈላጊ ግጭቶችን በማስቀረት ሃገራችን ከዓለም ተወዳዳሪ ማድረግ ከሁላችንም የሚጠበቅ ነዉ ብለዋል፡:

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባዔ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በበኩላቸዉ በዓሉ በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ሲከበር መቆየቱና በዚህም በብዝሃነት ላይ የተመሰረት የማንነቶች ትዉዉቅና ብዝሃነትን በኢኮኖሚ ዘርፉ የመዋዕለ-ንዋይ አንቀሳቃሽ በማድረግ፤የለውጥ እሳቤያችን ውጤትና የሰው-ተኮርነት ማሳያ የሆነውን የበጎ ፍቃድ መልካም ስራዎችን በተግባር በማሳየት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን በሁሉም ዘርፍ በማጠናከር በትኩረት ለዉጥ ያመጣንባቸዉ ነዉ ብለዋል፡፡

በዚህ ታላቅና ታሪካዊ በዓል የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የተለያዩ ባህላዊ አልባሳት፤ ምግቦች እና ባህላዊ ጭፈራዎች የዝግጅቱ ልዩ እንዲሁም የከተማዋን የልማትና የሰው ተኮር ተግባራት የሚያሳይ የስዕል አውደ ርእይ ድምቀት እንደነበሩ ተመላክቷል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.