እንዲህ ዓይነት ቤትና ክብር በህይወቴ አያለሁ ብዬ አስቤም አላውቅም፣ አሁን ግን ሆኗል" የካዛንቺስ የልማት ተነሺና የገላን ጉራ ነዋሪዋ ምስክርነት
ወይዘሮ ትርሃስ ተኪኤ ይባላሉ የቀድሞው ካዛንቺስ ተነሺ የአዲሱ የገላንጉራ ነዋሪ ናቸው።
ወይዘሮዋ በልማት ምክንያት ለበርካታ ዓመት ከኖርኩበት ካዛንቺስ ልትነሺ ነው ስባል ሰማይ ምድሩ የተደፋብኝ መስሎኝ ብዙ ቀን ተጨንቄያለው ብለውናል።
በዚህ ጭንቀት ውስጥ እያለሁ ጭራሽ ቤታችሁ ስለሚፈርስ ኑ ምትክ ቤት እጣ አውጡ ሲባል ጭንቀቴ በጣም ጨመረ ። ግን የማይቀር መሆኑን ስረዳ ወረዳ ሄጄ እጣ አወጣሁና የደረሰኝን ቤት ለማየት ቸኩዬ ሄጄ ሳየው ፈፅሞ ያልጠበኩት ሆኖ ሳገኘው እራሴን ማመን አልቻልኩም አሉን ወይዘሮ ትርሃስ።
ምክንያቱን ደግሞ ሲነግሩን ወይዘሮ ትርሃስ የደረሰኝ ቤት ሰፊና ፈረስ የሚያስጋልብ ሆኖ ማግኘቴ ነው ።
የደስታዬ ምክንያት ይህ ብቻ አይደለም ያሉት ወይዘሮ ትርሃስ ከቤት ስጦታው ባሻገር እቃችንን ጭነውና አጓጉዘው ምንም ባላወጣንበት በዚህ ሰፊ ቤት ማስገባታቸውና የተደረገልን መስተንግዶ ጭምር ነው ብለውናል።
ወይዘሮ ትርሃስ አሁን ያሉበትን ሁኔታም "እድለኛ" በማለት ገልፀው ልማት እንዲህ ሲፈጥንና ህዝብን ሲጠቅም በእድሜዬ ያየሁት ለመጀመሪያ ጊዜያቸው መሆኑን አጫውተውናል።
ትምህርት ቤቱ፣ ጤና ጣቢያው፣ ሸማቹ፣መሰረተ ልማቱ ፣ውሃው መብራቱ ተሟልቶ በሰፊው ቤቴ በደስታ እየኖሩ እንደሆነም ሳይሰስቱ ነግረውናል።
እንዲህ ሰውን ያማከለ ልማት የሚበረታታ ነውና ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ የዝግጅት ክፍላችን ያሳስባል። መልዕክታችን ነው።
ለበለጠ መረጃ
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.