ከተለያዩ የሃገራችን ከተሞች የተውጣጡ ከንቲባዎች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከተለያዩ የሃገራችን ከተሞች የተውጣጡ ከንቲባዎች በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል::

አዲስ አበባ ፕሮጀክት ጀምሮ በማጠናቀቅ ፣በአመራር ቁርጠኝነት እና ከህዝብ ጋር ተቀራርቦ እየተመካከሩ ስራዎችን በመስራት ትልቅ ልምድ የሚቀሰምባት መሆንዋን ገልፀው የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ የከተማዋን ገፅታ የሚቀይሩ እና የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ትላልቅ ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን በጉብኝቱ ወቅት መታዘባቸውን ከንቲባዎቹ ገልፀዋል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባ ላይ ለውጥ ለማምጣት የቻልነው ዋናው የአስተሳሰብ ለውጥ በማድረጋችን ነው ያሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከተሞች ከፕላን ውጪ ሲገነቡ ችላ በመባሉ ዛሬ በከተማ መዋቅራዊ ፕላን መሰረት የልማት ስራዎችን ለመተግበር መሰናክል ስለሆነብን እኛም

ዛሬ ተመሳሳይ ስህተት እንዳይፈጠር ከተማችንን እንደ ስሟ አዲስ እና አበባ ለማድረግ በከተማዋ ስታንዳርድ ልክ በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል::

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ወ/ሮ አለምጸሃይ ጳውሎስ በበኩላቸው ስራው እንደ ሃገር መስፋት ስላለበት እይታችንን በማስፋት ከተሞችን ውብ ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ማድረግ አለብን ያሉ ሲሆን አንድ ከተማ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ከተማ ልክ የሆኑ ተጨማሪ ከተሞችን መገንባት ይጠበቅብናልም ብለዋል::

የከተማ አመራሮችና ከንቲባዎች መሰጠትን ፣ ቆራጥነትን እና የምንናገረውን በተግባር መለወጥን ከአዲስ አበባ ተሞክሮ በመውሰድ ለህዝብ የገባነውን ቃል በመተግበር የህዝቡን ችግር የሚቀርፉ ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚጠበቅባቸው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.