ከካዛንቺስ ልትነሳ ነው ስባል እጅጉን አዝኜ ነበ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከካዛንቺስ ልትነሳ ነው ስባል እጅጉን አዝኜ ነበር፣ አሁን ግን ገላን ጉራ በመምጣቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ" የካዛንቺስ የልማት ተነሺና በገላን ጉራ በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ነዋሪ ምስክርነት

አቶ አሰፋ በለጠ የቀድሞ ካዛንቺስ ግቢ ገብርኤል አካባቢ በንግድ ስራ የሚተዳደሩ ነበሩ።

የኮሪደር ልማት ስለመጣ ከካዛንቺስ ልትነሱ ነው ሲባል በሁለት ምክንያት መሬት የተደፋብኝ ያህል ደንግጬ ነበር። የመጀመሪያው ከምተዳደርበት የንግድ ስራ ብፈናቀል እንዴት እሆናለው በሚል፣ በሁለተኛ ደረጃ ለዘመናት አብሬ ከምኖረው ማህበረሰብ መለያየቱ አስግቶኝ ብለውናል ።

ዛሬ ግን የከተማ አስተዳደሩ በሰጠን ትኩረት ያ ሁሉ ስጋቴ ጠፍቶ በደስታ መኖር ጀምሬያለው። ለዚህ ደግሞ ትልቁ ምክንያቴ ከካዛንቺስ በልማት ምክንያት ብንነሳም በክብር ሸኝተውን መኖሪያ ቤትና የንግድ ቦታ ስለሰጡን ነው ይላሉ አቶ አሰፋ ።

እንደካዛንቺስ ተነሺ እድለኛ አለ ብዬ አልገምትም ያሉን አቶ አሰፋ ለዚህ እንደ ምክንያት የሚያነሱት ደግሞ ሁሉም ነገር ወደተሟላበት ቦታ መጥተን ኑረችንንም ስራችንንም በአግባቡ እየሰራን በመሆናችን ብለዋል።

ለዚህም የከተማ አስተዳደሩን አመሰግናለሁ ያሉት አቶ አሰፋ በቀጣይ በተሰጣቸው የንግድ ቦታ ጠንክረው በመስራት እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን የመለወጥ ራዕይ መሰነቃቸውን አጫውተውናል።

ዛሬ ላይ በተሰጣቸው የመስሪያ ቦታ የአትክልትና ፍራፍሬ ንግዳቸውን እያጧጧፉት እንደሆነ ማስተዋል ችለናልና እንዲህ ዓይነት የሰው ልማትን መሰረት ያደረጉ ልማቶች ተጠናክረው ይቀጥሉ። መልዕክታችን ነው።

ለበለጠ መረጃ

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.