በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የኡራኤልና የፒኮክ አካባቢ የግል ባለይዞታ የወንዝ ዳር ልማት ተነሺዎች የካሳ ክፍያ መርሐ ግብር እንደቀጠለ ነው።
ተነሺዎቹ በግል ይዞታ የሚኖሩ ሲሆን ከዚህ በፊት የልማት ተነሺዎች ግልፅና ይፋዊ በሆነ መልኩ እጣ ምትክ ቦታ እጣ ማውጣታቸው ይታወቃል።
በዛሬው እለትም የግል ባለይዞታዎች በቦታና ቤት ግምታቸው መሰረት የካሳ ክፍያ እየወሰዱ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ነገን ጨምሮ የካሳ ክፍያው የሚቀጥል መሆኑም ተገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ በኮሪደር ልማት ከተማዋን ከማስዋብ ባሻገር የህዝቡን አኗኗር ባህል እየቀየረ ስለመሆኑ የልማት ተነሺዎቹ እጣ አወጣጥና የካሳ ክፍያ አንዱ ማሳያ መሆኑን በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.