በመዲናዋ ሁለተኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በነገው እለት ሊጀምር ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ሁለተኛ ዙር የህጻናት የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
የክትባት ዘመቻው ከታህሳስ 3 እስከ 6/2017 ዓ.ም ለ3ተከታታይ ቀናት በጤና ተቋማት፣በቤት ለቤት እና በትምህርት ቤቶች ክትባቱ ይሰጣል ተብሏል፡፡
ሁለተኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እድሚያቸዉ ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ 692 ሽህ ህጻናት የሚሰጥ ሲሆን የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ነገ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጤና ጣቢያ እንደሚጀመር ተገልጻል፡፡
በአንደኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት የተሰጣቸው ህጻናት ሁለተኛው ዙር የፖሊዮ ክትባት እንደሚሰጣቸውም ከአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.