የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስሩ የሚገኙ ተቋማትን በማዘመን አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ ነው፡- ፍጹም አሰፋ ( ዶ/ር )
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስሩ የሚገኙ ተቋማትን በማዘመን አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል እያደረገ የሚገኘው ጥረት የሚበረታታ ነው ሲሉ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክትር ፍጹም አሰፋ ተናገሩ፡፡
ዶክተር ፍጹም አሰፋና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ ( ዶ/ር ) የሚገኙበት የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እያከነወነ የሚገኘውን የሪፎርም ስራ ጎብኝቷል፡፡
ባለፉት አመታት በከተማዋ የነበረው የመሬት ልማት አስተዳደር አሰራር ለመልካም አስተዳደር ችግሮች የተጋለጠ በመሆኑ ከተማዋ የሚገባትን ጥቅም እንዳታገኝ አድርጓት መቆየቱን ቢሮው ባቀረበው ገለጸ አስታውቋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ይህንን ቸግር በጥናት በመለየት የሪፎርም ስራዎች እንዲከናወኑ ማድርጉን የተገለጸ ሲሆን በተለይም በቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ግንባታ፤ በመሬት አግልግሎት ሲስተም ልማት፤በመረጃ ዲጂታላይዜሽ አስተዳደር ስርአት ፤በተቋም አደረጃጃት እና ሲስተም ማሻሻል፤በቅንጅታዊ አሰራር፤ ምቹ አከባቢን በመፍጠር ላይ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸው ተመልክቷል ፡፡
በአሁኑ ወቅትም የከተማ መሬት በዘመናዊ መረጃ ቋት ውስጥ እንዲቀመጥ ማድርግ ተችሏልም ተብሏል፡፡
የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ ( ዶ/ር ) መሬትን የኢኮኖሚ ምንጭ ለማድርግ እንደሀገር እየተሰራበት መሆኑን ያነሱ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ እሮሮ ይበዛበት የነበረውን የመሬት ልማት አስተዳር ቢሮን አሰራር ማዘመኑ የሚያስመስገነው መሆኑን አንስዋል፡፡
ይህ ልምድም በሌሎች ክልሎች ተወስዶ ተግባራዊ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የፌደራል ሱፐርቪሽን ቡድን ከሰሞኑ የአድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ በተለያዩ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ተቋማት ያሉበትን ደረጃ መመልከቱን አንስተዋል፡፡
በከተማዋ እየተሳኩ ለመጡ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት እንዲቻል ለማድርግም በሪፎርሙ እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት የአመራሩን ቁርጠኝነት ያመለከቱ ናቸው ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.