የአፍሪካ መዲና እና የፅናት ተምሳሌት የሆነችው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአፍሪካ መዲና እና የፅናት ተምሳሌት የሆነችው አዲስ አበባ ዘመናዊነቷ ጎልቶ እየታየ ነው!!

በደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ትምህርት ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ቡሳኒ ንግካዌኒ ዴይሊ ማቭሪክ ለተሰኘ በደቡብ አፍሪካ ለሚዘጋጅ መጽሔት እንዳሉት የአፍሪካ መዲና እና የፅናት ተምሳሌት የሆነችው አዲስ አበባ ዘመናዊነቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጎልቶ እየታየ ነው።

ቡሳኒ ንግካዌኒ አዲስ አበባ እንደ ደርባን፣ ሉዋንዳ፣ ሞምባሳ እና ኪንሻሳ ላሉ ከተሞች የልማት እና የዕድገት ምልክት እየሆነች መምጣቷን ባሰፈሩት ትንታኔ ገልጸዋል።

በመዲናዋ እየተገነቡ ያሉ ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን በአድናቆት እንደሚያዩ የገለጹት ምሁሩ፣ በፈተናዎች ውስጥ ማደግ፣ በተቃርኖዎች መካከል መታደስ የሚታይባት እንደነ ካይሮ እና ኬፕታውን ዕድገት እና ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ያለች ከተማ ናት ብለዋል።

የአዲስ አበባ ለውጥ ጎልቶ የሚታይ መሆኑን እማኝነታቸውን ያስቀመጡት ቡሳኒ ንግካዌኒ፣ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች ከቀያቸው መለወጥ ጋር በተያያዘ በዋጋ ንረት እና በትራንስፖርት እጥረት እንዳይቸገሩ በማድረግ ለውጡን በስኬት እየመራች መሆኑን መታዘባቸውን ነው የገለጹት።

መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት እና በመሠረተ ልማት ግንባታው ከተማዋ ሌላ ማራኪ ገፅታ እንድትላበስ እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።

ብልህ እና ታታሪ የሆነው የከተማዋ አስተዳደር በመዲናዋ ከሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ከንቲባ ጽ/ቤት ያለው መንገድ ፅዳቱን የጠበቀ እና በሥርዓት የተሰደረ እንዲሆን መደረጉን መታዘባቸውንም ጠቁመዋል።

ከእያንዳንዱ አስፋልት ሥር አዳዲስ የውኃ ቱቦዎች እና የፋይበር ኦፕቲክ ኬብሎች መዘርጋታቸውን አመልክተው ይህም የከተማዋን ዕድገት ቀጣይነት ያመለክታል ብለዋል።

የከተማዋን ነዋሪዎች፣ የባንኮች እንዲሁም የኤምባሲዎችን ድንበር እና ግድግዳ በመግፋትም ጭምር እየተገነባ ያለው የአስፋልት መንገድ የትራፊክ መብራቶች እና አደባባዮች የተካተቱበት፣ ከመኪና በተጨማሪ የሳይክል እና የእግረኛ መንገድ ያሉት መሆኑንም መመልከታቸውን ነው ሐሳባቸውን ያሰፈሩት።

የአዲስ አበባ የዕድገት መሠረት የሆኑት ነዋሪዎቿ መሆናቸውን የሚገልጹት ምሁሩ፣ የመዲናዋ ጎዳናዎች የደከመ ጉልበትን የሚያበረቱ፣ ሕይወት የሚዘሩ መሆናቸውን መስክረዋል።

እንደ ስሟ አዲስ የትውልድ ሀገር ልትሰኝ የምትችልም ሆናለች ሲሉ አስተያየታቸውን አጠቃለልዋል።

ቡሳኒ ንግካዌኒ:- የደቡብ አፍሪካው ምሁር ናቸው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.