ቃልን በተግባር...!

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ቃልን በተግባር...!

የፓርቲያችን ምክትል ፕሬዝዳንት እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራው የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙና መጠነሰፊ የተቀናጁ የልማት ተግባራትን ተመልክተናል።

የአኗኗር ዘይቤን ያሻሻሉ፣ ፍትሐዊነትን የሚያረጋግጡ፣ አዳዲስ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማካሄድ ያስቻሉ፣ መነሻና መድረሻቸው ሰው ተኮር የሆኑ፣ ሰፋፊ የሥራ ዕድል የፈጠሩ፣ በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት የተከናወኑ፣ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ድንቅና ስኬታማ ተግባራትን ተመልክተናል።

ከተማዋን ፅዱ፣ አረንጓዴና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት የብልፅግና ዕሳቤዎች ወደ ተግባር የተቀየሩበት፣ የአመራር ትጋት፣ ቁርጠኝነትና ፅናት የታየበት የህዝብ የመልማት ፍላጎት የተረጋገጠበት ሲሆን ክብርት ከንቲባና የሥራ ባልደረቦቻቸው ያሳዩትን ትጋት ላደንቅ እወዳለሁ።

የሰሩ እጆች ሁሉ ብሩክ ይሁኑ!

የስራ እና ክህሎት ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.