ክልሎች ከአዲስ አበባ በጥራትና ፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት እየበቁ ከሚገኙ የልማት ስራዎች ትምህርት በመውሰድ ለዜጎች ተጠቃሚነት መስራት ይጠበቅባቸዋል:: የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ
በአዲስ አበባ የሚከናወኑ የኮሪደር፣ የወንዝ ዳር እና የመልሶ ማልማት የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች ከተማዋን የሚያስውቡና የህዝብን ተጠቃሚ ያረጋገጡ ናችው ብለዋል::
በተለይም የኮሪደር ልማት ስራው የመዲናዋን ዕድገት በማሳለጥ ለዜጎች ዘመናዊ የከተሜነት አኗኗር ዘይቤን የሚፈጥር ነው ብለዋል።
የመንገድ፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የውሃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የመኖሪያ ቤት፣ የቴሌኮሙኒኬሽንና መሰል የመሰረተ ልማት ግንባታ ተግባራቱም ለቀጣዩ ትውልድ ምንዳ መሆናቸውን አንስተዋል።
የካዛንችስ የልማት ተነሽ ዜጎች የተሻለ ሕይወት የሚመሩበት የገላን ጉራ የልማት መንደርም በተሰናሰለ የመሰረተ ልማት ግንባታ በጥራትና ፍጥነት የተጠናቀቀ መሆኑን በምልከታ እንዳረጋገጡ አስረድተዋል።
በአጠቃላይ የብልጽግና ፓርቲ በመዲናዋ እያከናወነ የሚገኘው የመሰረተ ልማት ግንባታ አዲስ አበባን ጽዱ በማድረግ ለአፍሪካ ምሳሌ የሆነች ከተማ መፍጠር የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል።
በወንዞች ዳርቻ እየተከናወነ ያለው ልማት ንጹህ አካባቢን ለመገንባት የሚያስችልና ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
የመዲናዋ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎችም የብልጽግና ፓርቲ መገለጫ ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ፥ በቀጣይም ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን የሚያላብሱ ውጤታማ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በማስፋት ለህብረተሰብ ተጠቃሚነት በትጋት ይሰራል ብለዋል።
ክልሎች በመዲናዋ በጥራትና ፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት እየበቁ ከሚገኙ የልማት ስራዎች ትምህርት በመውሰድ ለዜጎች ተጠቃሚነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.