የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት የታሪክ እና የባሕል ቅርሳችንን ጠብቆ ለማቆየት የምናደርገው ጥረት ከፍ ያለ ርምጃ ነው።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጀመረው የእድሳት ተግባር አሁን አንድነት ፓርክ ከሆነው ከታላቁ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ጀምሮ ይኽን ትእምርታዊ ስፍራ እንደገና ለታላቅ አገልግሎት እንዲሰናዳ በማድረግ ቀጥሏል። ብሔራዊ ቤተመንግሥት አሁን የሕዝባችንን ጽናት፣ ጥበባዊ አቅምና ርዕይ ግዘፍ ነስቶ የሚታይበት የሀገራዊ ጉዟችን ዋቢ ሆኖ ይታያል። የቀደመ ግዝፈቱን እና ውበቱን በመመለስ ያለፈ ታሪካችንን እናከብራለን። ለትውልዶችም የኩራትና የተነሳሽነት ዘላቂ ተምሳሌት አኑረናል።
እንሆ የቤተመንግሥት ሙዝየም ለሁሉም ሆኗል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.