የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻን በይፋ አስጀምሯል ።
የክትባት ማስጀመሪያው በአራዳ ክፍለከተማ መስከረም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እና የክፍለከማው የስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታሁን አበራ ፤ የቢሮው የማኔጅመንት አባላት እና ባለሙያዎች ባለድርሻ አካላት እና የሃይማኖት መሪዎች ፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች በተገኙበት ተጀምሯል ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ የማህጸን በር ካንሰር በሽታ በሴት እህቶቻችን ብሎም በማህበረሰቡ ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በመረዳት እና ይህን የከፋ የጤና ችግር መከላከል ይቻል ዘንድ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረው
በሽታውን ከምንከላከልባቸው የተለያዩ ስልቶች አንዱ ታዳጊ ሴት ልጆችን በት/ቤት እና ከት/ቤት ውጭ ክትባት እንዲያገኙ ማድረግ ሲሆን ክትባቱን በሀገራችን ብሎም በከተማችን የሚመለከታቸውን ታላሚዎች ተደራሽ ማድረግ ከጀመርንበት 2011 ዓ.ም አንስቶ በርካታ ሴት ልጆች የክትባቱ ተጠቃሚ መሆናቸውንም ዶክተር ዮሐንስ በማስጀመሪያው አመልክተዋል፡፡
በክትባት ዘመቻው 177,933 ለሆኑ ታዳጊ ሴት ልጆች ክትባቱን እንዲወስዱ መታቀዱን እና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በየክ/ከተማውና ጤና ጣቢያዎች በበቂ መጠን የደረሰ ሲሆን 381 የክትባት ቡድኖችን በማዋቀርና የሚመለከታቸው ሁሉ በት/ቤቶችና ከት/ቤት ውጭ የሚገኙ ሴት ልጆችን ከዛሬ ታህሳስ 21ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ስለሚሰጥ ለስኬታማነቱ ሁሉም እንዲተባበር ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው ዛሬ በማለዳ በመስከረም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስጀመርነው የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባ በሁሉም የመንግስት እና የግል ት/ቤቶች ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን ይሰጣል ።
ለዚህ ክትባት ስኬት የትምህርት አመራሩ አጠቃላይ ወላጆች እና የትምህርት ማህበረሰቡ እድሜቸው ከ9እስከ 14አመት ያሉ ሁሉ ክትባቱን በመውሰድ ጤናቸውን ከዚህ አስከፊ በሽታ እዲጠብቁ አደራ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
አዲስ አበበ ጤና ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.