መጪውን በዓል ህብረተሰቡ በሰላምና በተረጋጋ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

መጪውን በዓል ህብረተሰቡ በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲያከብር ግብረ ሀይሉ የሚያደርገውን ክትትልና ቁጥጥር አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የግብረ ሃይል ሰብሳቢ

የገበያ ማረጋጋት፣ገቢ መሰብሰብ፣ ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ፣ የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ግብረ ሀይል የስራ አፈጻጸሙን እና ለሚያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች መፍትሄ ለማበጀት ውይይት አድረጓል።

ውይይቱን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የግብረ ሃይል ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ መጪውን በዓል ህብረተሰቡ በተረጋጋ መልኩ እንዲያከብር የግብይት ቦታዎችን በማመቻቸት እና የምርት አቅርቦትን በመጨመር ግብረ ሀይሉ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

አቶ ጃንጥራር አክለውም የባዛር ቦታዎች ለህብረተሰቡ ምቹ በማድረግ፣ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር በቅንጅት መስራት እንዲሁም ስራዎችን በየጊዜው መገምገምና ለሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ ሰጪ በመሆን ግብረሀይሉ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።

የግብረ ሀይሉ አባላት በቀረበው የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ስራዎችን በተሰጡ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የተሰሩ በመሆኑ የምርት አቅርቦት ተደራሽነት በማስፋት፣ የመስሪያ ቦታ በማመቻቸት፣ ህግን በማስከበር፣ የገቢ አሰባሰብ በመጨመር የእሁድ ገበያን በስታንዳርዱ መሰረት በማስፋት የተሰሩ ስራዎችን በተግባቦት በማስደገፍ ላይ አዳጊ ውጤት መታየቱን ጠቁመዋል ።

የንግድ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው ለመጪው በዓል የግብዓት አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር በቂ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመው የአቅርቦትና የዋጋ ጭማሪ እንዳይፈጠር የሚደርገውን ክትትልና ቁጥጥር በማጠናከር በትኩረት መስራት የግብረሀይሉ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ነው ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.