"የበዓላት ወቅትን አስመልክቶ የምርት እጥረት እ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የበዓላት ወቅትን አስመልክቶ የምርት እጥረት እንዲሁም የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ባዛሩ ወሳኝነት አለው "የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ

የቢሮ ኃላፊዋ ይህን ያሉት በዛሬው እለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ባዛር መከፈቱን ተከትሎ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተገኙበት የገና በኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ ነው።

በዛሬዉ ዕለት በሁሉም ክፍለ ከተሞች መጪውን የገና በአል በተመለከተ ለከተማችን ነዋሪዎች የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር እንዲሁም የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ያለመ ኤግዚቢሽን እና ባዛር በዚህ ወቅት በየክፍለ ከተማ መከፈቱ ለማህበረሰቡ ወሳኝ መሆኑ ተናግረዋል።

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ለገና በአል የተከፈተው ኤግዚቢሽን እና ባዛር የግብርና እና የእንሰሳት ተዋፅኦ ዉጤቶች፤ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ጨምሮ ሌሎችም አስፈላጊ ግብዓቶች በህብረት ስራ ዩኒየኖች በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ ፤ጥራትና ልክ ለሸማቹ የህብረተሰብ ክፍል እየቀረበ የሚገኝ መሆኑ ታዉቋል፡፡

በኤግዚቢሽና ባዛሩ ላይ አምራች ኢንተርፕራይዞች ፤የህብረት ስራ ማህበራትና የተለያዩ አንቀሳቃሾች በስፋት የተሳተፉበት ሲሆን እስከ በዓሉ ዋዜማ ክፍት ሆኖ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በሁሉም ክፍለ ከተሞች የኤግዚቢሽን እና ባዛር መርሀ ግብሩን ሲከፈት የከተማ ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በጋራ ተገኝተዉ አስጀምረዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል እንዲቻል ባማመቻቻቸዉ የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማእከላት እንዲሁም መጪዉን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በይፋ ከተከፈተዉ ኤግዚቭሽ እና ባዛር ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍል በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪዉን ያቀርባል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.