በመዲናችን አዲስ አበባ መጪው የገና ባአልን ምክንያት በማድረግ በተከፈቱ ባዛሮች ግብይቱ በደመቀ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።
በሁሉም ክፍለ ከተሞች የገና በአልን ምክንያት በማድረግ በተከፈቱ የባዛር እና ኤግዚቢሽን የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በስፋት መቅረባቸውንና የግብይት ሂደቱም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ከተጠቃሚዎች እና አምራቾች ጋር በተደረገዉ የገበያ ቅኝት ለማወቅ ተችሏል።
በመገበያያ ስፍራዎቹ አምራች ኢንተርፕራይዞች ፤ የህብረት ስራ ማህበራትና የተለያዩ አንቀሳቃሾች በስፋት እየተሳተፉ መሆኑም ታዉቋል፡፡
የገበያ ማረጋጋት ፣ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር፣የአዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ግብረ-ሀይል በአሉን አስመልክቶ ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ ተቋማት ተቀናጅተው በመስራት ማህበረሰባችን በበአል ወቅት ከሚደርስበት የተጋነነ የዋጋ ንረት እና የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር መሰራት እንዳለበት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የተጠናከረ ስራ እየተሰራ መሆኑ ታውቋል።
የበአል ባዛሩን በተመለከተ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ቅኝት ተደርጎል።በቀጣዮቹ ቀናትም የገበያ ስርዓት ሰንሰለቱ በተጠናከረ መንገድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፤ሁሉንም ማህበረሰብ ባማከለ መልኩ ያለምንም ችግር በአሉን እንዲያሳልፍ ለማድረግ ፣ አርሶ አደሮችና የኢንዱስትሪ ምርት አቅራቢዎች ምርታቸዉን በሰፊዉ የሚያቀርቡበትና ዩኒየኖችና ህብረት ስራ ማህበራት ይበልጥ የሚሳተፉበት የርብርብ ስራ እየተከናወኑ መሆኑ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.