የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ዕድገት 11 በመቶ ለ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ዕድገት 11 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነው ፡- አቶ ጃንጥራር አባይ

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ዕድገት 11 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አስታወቁ።

ምክትል ከንቲባው የዘንድሮውን የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄን በኮልፌ ቀራኒዮ እና የካ ክፍለከተሞች አስጀምረዋል።

ኢትዮጵያን ከሸማችነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር እንዲሁም በመፍጠርና በማምረት ቀጣይነት ያለው ዕድገትና ብልፅግና ለማረጋጥ ባለፉት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዘንድሮም በሁሉም ክፍለ ከተሞች በይፋ ተጀምሯል።

3ኛ ዓመቱን የያዘው ንቅናቄው የአምራቾችን አቅም በማጎልበትና ችግሮችን በመፍታት ምርታማነትን ከፍ ያደረገ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው የአምራች ኢንዱስትሪውን ዕድገት 11 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነውም ብለዋል።

ንቅናቄው አምራቾች ያሉባቸውን ችግሮች የሚያሰሙበት እና መፍትሔ ለማበጀት ዕድል የሚሰጥ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው ለኢንዱስትሪዎች የሚደረግ ድጋፍ ለሀገር ዕድገት ትልቅ አበርክቶ ስላለው በመንግስት በኩል ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ንቅናቄው በፈጠረው ተነሳሽነት ባለፉት ዓመታት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የሚተኩ ምርቶች በክፍለ ከተማችን ተመርተዋል ያሉት የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ በቀጣይም ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚሰጠው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የየካ ክፍለ ከተማም በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የበርካታ አምራቾችን አቅም ማሳደግና የገበያ ትስስር መፍጠር መቻሉን የገለፁት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ ከአምራቹ ጋር በቅርበት መስራት እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪዎች ዕድገት አሁን ላይ 8 ነጥብ 2 የደረሰ ሲሆን ንቅናቄው ከመጀመሩ በፊት ከ7 በመቶ በታች እንደነበርም ተመላክቷል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.