በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በየካ ክፍለ ከተማ ከቀበና ድልድይ ጀምሮ እየለማ የሚገኘዉን የወንዝ ዳርቻ ልማት የደረሰበትን ደረጃ ምልከታ አደረጉ!!

የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በየካ ክፍለ ከተማ ከቀበና ድልድይ ጀምሮ እስከ እንጦጦ ተራራ ሐምሌ 19 የሚለማውን የቀበና የወንዝ ዳርቻ ልማት የደረሰበትን ደረጃ ከከተማ አመራሮች፣ ከየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ከአቶ ብርሃኑ ረታ፣ ከክ/ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ምልከታ አድርገዋል።

ፕሮጀክቱን በበላይነት የሚያስተባብሩት አቶ ሞገስ የወንዝ ዳርቻ ልማቱ የደረሰበትን ደረጃ ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው ቦታዎች ተዘዋውረው ምልከታ በማድረግ አበረታትተዋል።

የወንዝ ዳርቻ ልማቱ ከተማዋን ውብና ፅዱ ከማድረጉ ባሻገር ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመገንባት የጎላ ሚና እንዳለው አመላክተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.