ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ መልዕክት 2ኛው የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ መልዕክት 2ኛው የብልፅግና ፓርቲ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ውይይት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የኢንስፔክሽንና ሥነ ምግባር ኮምሽን ባቀረበው ረቂቅ ሪፖርት ላይ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እሳቤዎች እና ልምምዶችን በተለወጠ እና አዲስ የሆነ የስራ ባህል በመተግበር የነዋሪውን ህይወት መለወጥ ያስቻሉ ስኬቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡

ፓርቲው ከምስረታው ጀምሮ በሁለንተናዊ መስኮች ለውጦችን ለማምጣት የህዝቦችን ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የገባውን ቃል ከስኬት ለማድረስ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

ከነባር እሳቤዎች በመውጣት ተጨባጭ ለውጥ ያመጡ አሰባሳቢ እና አሳታፊ የፖለቲካ እሳቤን በመተግበር፣ የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚን ስርዓትን ወደ ስራ በማስገባት፣ በሰው ተኮር ተግባራት እና በአጠቃላይ ማህበራዊ ዘርፎች የህዝቦችን ተጠቃሚነት ቅድሚያ በመስጠትና በማረጋገጥ፣ ፕሮጀክቶችን አቅዶ በፍጥነት በመተግበር እና ወደ ስራ በማስገባት፣ ስኬታማ ዲፕሎማሲን በማካሄድ እና በመሰል መስኮች ቃል በተግባር የተለወጠበት እና አዲስ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ባህል ለውጥ መምጣቱን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች ብልጽግና ፓርቲ በአንደኛው ጉባኤው የገባቸውን ቃሎች በተጨባጭ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ለቀጣይ ሶስት ቀናት በሚካሄደው የቅድመ ጉባኤ ውይይት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል ብሎም የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ለማረም በሚያስችል ደረጃ በጥልቀት የሚወያዩ ይሆናል፡፡

የቅድመ ጉባኤ ውይይቶችና የአባላት ኮንፍረስ እስከ ጉባኤው መዳረሻ ድረስ በድምቀትና በከፍተኛ መነሳሳት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/addisababacommunication

 

 

 

 

 

 

 

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.