ከቻይናዋ ጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ሹ ኩንሊን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ሚስተር ሹ ኩንሊን በህዳር ወር በአዲስ አበባ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የጂያንግሱ ግዛትን እንድንጎበኝ ባቀረቡልን ግብዣ መሰረት በግዛቱ ጉብኝት በማድረግ ላይ የምንገኝ ሲሆን፣ በጉብኝታችን ወቅት ከጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ እና አመራሮች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በመወያየት በቀጣይ በጥቅሉ በኢንቨስትመንት ፣ በንግድ ፣ በቱሪዝም ፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፎች ላይ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና በቀጣይም በትብብር ለመስራት ተግባብተናል።
ሚስተር ሹ ኩንሊን በጂያንግሱ ግዛት በነበረን ጉብኝት ላደረጉልን መስተንግዶ ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.