በምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ፕሮግራም የስራ እድል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ፕሮግራም የስራ እድል አግኝተው ሲሰሩ የነበሩ ከተረጂነት ወደ አምራችነት የተሸጋገሩ 31ሺ 2 የከተማችንን ነዋሪዎች አስመርቀናል።

የከተማችን ነዋሪዎች ሰርቶ በመለወጥ፣ በትጋት፣ የተገኘውን እድል ወደ ድል በመቀየር፣ ኑሯቸውን በማሻሻል እና ከተረጂነት በመላቀቅ አምራች ዜጋ እና ተወዳዳሪ በመሆን ከራሳችሁ አልፋችሁ ለሌሎች ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ተተኪ የሌለው ሚናችሁን እንድትወጡ ጥሪ አቀርባለሁ።

ከተረጂነት ወደ አምራችነት የተሸጋገራችሁ ነዋሪዎቻችን ኑሯችሁን በራሳችሁ አቅም በዘላቂነት ለመምራት በመቻላችሁ እና ለምረቃ በመብቃታችህ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ ከጥር 1 ጀምሮ በመንግስት በጀት 154 ሺሕ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የምናደርግ ሲሆን ማህበራዊ ፍትህን በማረጋገጥ ለብዙ ዘመን አንገት ያስደፋንን እና ለተረጂነት የዳረገንን ድህነትን በማሸነፍ በልተን ማደር ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋጥ በትጋት የምንሰራ ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.