በላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ያስገነባውን የጋራ መኖሪያ ህንፃ ለነዋሪዎች አስተላለፈ

የበላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች ያስገነባውን የጋራ መኖሪያ ህንፃ ለነዋሪዎች አስተላልፏል::

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ከመዲናዋ ባለሀብቶች ጋር በመቀናጀት የነዋሪዎችን ህይወት ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የከተማዋ ባለሀብቶች በመዲናዋ ሁለንተናዊ ልማት እና የነዋሪዎችን ህይወት በማሻሻል ውስጥ ደማቅ አሻራቸውን እያስቀመጡ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

ባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በበኩላቸው፣ የዜጎችን ህይወት ለማሻሻል በቀጣይም በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

በጋራ መኖሪያ ቤቱ ግንባታ ወቅት ያላሳለሰ ጥረት ላደረጉ የመዲናዋ አመራሮችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

AMN

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.