በፌዴራል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር የተቋቋመው የሱፐርቪዥን ቡድን በከተማና በክፍለ ከተማ ደረጃ ሲያከናውን የነበረውን ምልከታዉ አጠናቀቀ።
በፌዴራል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር የተቋቋመው የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ እና በክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅ/ቤቶች ላይ ሲያከናውን የነበረውን
ሱፐርቪዥን በዛሬው እለት አጠናቀቀ።
ቡድኑ በእቅድ ዝግጅት፣ በይዘት ቀረፃ፣የሚዲያ ግንኙነት ፣የህዝብ ግንኙነት፣በዲጅታል ሚዲያ አጠቃቀምና ሞኒተሪንግ ዘርፍ እንዲሁም በጥናትና ምርምር ዘርፍን በአጠቃላይ በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ምልከታ አከናውናል።
በፌዴራል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳልካቸው ፀጋዬ በምልከታቸዉ እንደተናገሩት ጠንካራ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራ ለሀገረ መንግስት ግንባታ ሚናው ላቅ ያለ እንደሆነ ገልፀዉ ከተማዋን በሚመጥን መልኩ ለሌሎች ተሞክሮ መሆን የሚችል ሰፊ ስራዎች በአዲስ አበባ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተመለከትን ሲሆን ለሌሎች ክልሎች ጭምር ተሞክሮ ሊሰጥ በሚችል ደረጃ የተደራጀ የተግባቦት ሂደት መመልከታቸውን ገልፀዋል።
የሱፐርቪዥኑ ብድን አባላት በከተማው ፣በክፍለ ከተማው እንዲሁም በሴክተር ተቋማት የጋራ የተቀናጀና የተናበበ የተግባቦት ተግባር እጅጉን ያስደሰታቸው መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፣ የኮልፌ ቀራኒዬ ክፍለ ከተማ እና የልደታ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤቶች በመገኘት ሱፐርቪዥን ያካያኔዱ ሲሆን የጉለሌ ክፍለ ከተማ እስቱዲዬን ጉብኝት አድርገዋል ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.