"ከቃል እስከ ባህል " በሚል መሪ ቃል 2ኛው የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ከቃል እስከ ባህል " በሚል መሪ ቃል 2ኛው የብልፅግና ፓርቲ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ውይይት በሁሉም ክፍለ ከተማ ደረጃ እየተካሄደ ይገኛል ::

ውይይቱ የብልፅግና ፓርቲ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ በተመለከተ በክፍለ ከተማ ደረጃ ውይይቱ የቀጠለ ሲሆን በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባቀረቡት የቪዲዮ ማብራሪያና የውይይት መነሻ እንዲሁም የኢንስፔክሽንና ሥነ ምግባር ኮሚሽን ሪፖርት ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ታዉቋል፡፡

በዉይይቱም በየደረጃዉ ያሉ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች የተሳተፉበት ሲሆን ዛሬ የተጀመረው የቅድመ ጉባኤ ውይይት እስከ አባላት እንደሚወርድና የጉባኤው ኮንፍረንስ እስከ ዋናው ጉባኤ መዳረሻ ድረስ በድምቀትና በከፍተኛ መነሳሳት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.