በነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለሴተኛ አዳሪነት እና ለተለያዩ የማህበራዊ ችግሮች ተጋልጠዉ የነበሩ 400 እህቶቻችንን እና ሴት ልጆቻችንን ለሁለተኛ ዙር ስልጠና እንኳን ደህና መጣችሁ ብለናል።

በመጀመሪያ ዙር ስልጠና የወሰዱ ከ300 በላይ የሚሆኑ እህቶቻችን በ17 አይነት ዘርፎች የክህሎት እና ተሃድሶ ስልጠና ወስደዉ የሞያ ባለቤት ሆነዉ የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ።

በማህበረሰባችን ውስጥ ስር በሰደደ ኃላቀር አስተሳሰብ፣ ኢፍታዊነት፣ ፆታዊ ጥቃት እና ተጋላጭነት ምክንያት በእህቶቻችን እና ሴት ልጆቻችን ላይ የሚደርስ ማህበራዊ ስብራትን በመጠገን ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን የጀመርነውን ስራ በመደገፍ ከጎናችን የቆማችሁ የከተማችን ልበ ቀና ባለሃብቶችን፣ የቦርድ አባላት፣በሞያችሁ እየደገፋችሁን ያላችሁትን እንዲሁም ራዕያችንን ወደ መሬት ለማውረድ የደከማችሁ የማዕከሉ አመራሮችንና፣ ሰራተኞች ና መምህራንን በእህቶቻችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

የሁለተኛ ዙር ሰልጣኝ የሆናችሁ እህቶቻችን የማዕከሉ ቆይታችሁ እራሳችሁን የምትለውጡበት፣ ለቤተሰቦቻችሁ እንዲሁም ለሌሎች መለወጥ አርአያ የምትሆኑበት እንዲሆን አደራ እያልኩ የሚሰጣችሁን ስልጠና በትጋት በመከታተል እንደ መጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ስኬታማ እንድትሆኑ ጥሪ አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.