በቀን 30 ሚሊዮን ሊትር ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የቦሌ አራብሳ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::
ከለዉጡ ወዲህ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምሮ የመጨረሶ አንዱ ማሳያ የሆነዉ ይህ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የከተማችንን የፍሳሽ ማጣራት አቅም ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረበት በቀን 48 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ወደ በቀን233 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ከፍ ማድረግ አስችሎናል::
ይህ የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአካባቢውን ነዋሪዎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማጣሪያ ፣ስርዓት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ።
ለአንድ ከተማ ወሳኝ ከሆኑ መሰረተ ልማቶች መካከል የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓትን ማዘመን ትልቅ ስራ ሲሆን ጤንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ከመፍጠር አኳያ ያለው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡በመሆኑም ይህ የፍሳሽ ማጣሪያ ስራ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓታችንን የሚያዘምን፣ የከተማችን ነዋሪዎችን እና በአጎራባች አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎት የረዥም ጊዜ ቅሬታን ምላሽ የሚሰጥ ፣ከተማችንን ከብክለት የጸዳች፣ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ እዉንየሚያደርግ ነዉ።
ፕሮጀክቱ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ያደረጋችሁ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ኮንትራክተርና አማካሪ ድርጅት ክፍለከተማው ከምንም በላይ በፈቃደኝነት ለልማት ከቦታው የተነሱ አርሶ አደሮችን በነዋሪው እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.