በ 2ኛ ዙር የጀመርናቸው ስምንቱን የኮሪደር ልማት ስራዎቻችንን አፈፃፀም ከማለዳ ጀምረን ተዘዋውረን ገምግመናል::
አብዛኛዎቹ ስራዎቻችን በተያዘላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ ይገኛሉ ፤ ስራው በተያዘለት እቅድ መሰረት እንዲጠናቀቅ 24 /7 እየሰራችሁ ያላችሁ ሰራተኞች፣ እያስተባበራችሁ ያላችሁ አመራሮች፣ ቦታውን ለልማት በመልቀቅ ወደ ተዘጋጀላችሁ አዲስ ቦታ በፈቃደኝነት በመግባት የተባበራችሁ ዉድ ነዋሪዎቻችን እንዲሁም ማሽነሪዎቻችሁን ያለ ክፍያ ያበረከታችሁ እንዲሁም አካባቢያችሁን በማፅዳትና ህንፃችሁን በማደስ ከጎናችን የቆማችሁ ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ተባብረን ከተማ እየገነባን በመሆኑ ሁላችሁም የከተማችን ባለውለታዎች ናችሁ ።ለዚህም በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.