ለ340 የፓሊስ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት የመኖ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ለ340 የፓሊስ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤት በማስተላለፍ ቤት ለንቦሳ ብለናል።

2ኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ለመተግበር የፖሊሶችን ካምፕ ስንጎበኝ የሰራዊቱ አባላት ካምፕ ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው እና ከልጆቻቸው ጋር እጅግ በማይመች ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ መሆኑን በመረዳት ለነዋሪዎች እንዳደረግነዉ ሁሉ ለ340 ቤተሰብ ላላቸው የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤቶችን አስተላልፈናል።

ፖሊስ ቅድሚያ ለህዝብ እና ለሀገር ደህንነት ዋጋ እየከፈለ የሚያገለግል እንደመሆኑ መጠን በቀጣይም ለሰራዊቱ ምቹ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖረዉ ከተቋሞቻቸዉ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምንሰራ ይሆናል::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.