የጥምቀት በዓል አንድነታችንን፣በህላችንንና መልካም ገፅታችንን ለዓለም ሕብረተሰብ ከፍ አድርገን ከምናሳይባቸው የአደባባይ በዓሎች አንዱ ስለሆነ ልንጠብቀው ይገባል ተባለ::
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብክት ጋር በመተባበር ከደብር አስተዳ ዳሪዎችና የፀሐፊዎች ጋር የጥምቀት በዓል አከባበርን በማስመልከት የማጠቃለያ ውይይት አድርገዋል።
የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት የዘንድሮ የጥምቀት በዓልን ለየት የሚያደርገው ከዚህ ቀደምት ሲነሱ የነበሩ የታቦታት ማደሪያ ቦታዎች ችግሮች በኮሪደር ልማቱ ምክንያት ምቹና ሳቢ በሆነ መልኩ መፈታታቸው ነው ብለዋል።
የጥምቀት በዓል አንድነታችንን፣በህላችንንና መልካም ገፅታችንን ለዓለም ሕብረተሰብ ከፍ አድርገን ከምናሳይበቸው የአደባባይ በዓሎች
መካከል አንዱ ስለሆነ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ሚናውን እንዲወጣ አሳስበለሁ ብለዋል።
የዛሬው የማጠቃለያ መድረክ ዋና ዓላማ በዓሉ ታላቅ የአደባባይ በዓል በመሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ሰላምን የሚያደፈርሱ ጉዳዮች ላይ በቀጣይ በሚቀሩ ቀናቶች ውስጥ ትኩረት ተሰጥቷቸው መስተካከል እንዲችሉ የጋራ ግንዛቤ የሚወስድበትና ምክክር የሚደረ
ግበት መድረክ ነው ሲሉ የአዲስአበባየሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብክት ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ማህምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ፣የመወያያ ሰነድ ሲያቀርቡ፣በዓሉ ሰላማዊም መንፈሳዊም እንዲሆን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮምሽነር ጌቱ አርጋው በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት የጥምቀት ዓለም አቀፍ የአደባባይ በዓል እንደመሆኑ መጠን በዓሉን ለመታደም በርካታ ቱሪስቶች ወደ ሀገራችን ስለሚገቡ በተለየ ትኩረት መሥራት እንደሚያ
ስፈልግ ተናግረዋል።
ኮምሽነር ጌቱ አክለውም የፀጥታ ስራዎቻችን አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ በማለቱ ከምንም በላይ ቅድሚያ በመስጠት በዓሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.