"ከቃል እስከ ባህል! "
ብልፅግና በአዲስ የፖለቲካ እሳቤ እየተመራ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ባህል እየገነባ ይገኛል።
ፓርቲው እራሱን በማጠናከር ሀገረ መንግስት ግንባታውን ለማፋጠን ብርቱ እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን ለውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲም ልዩ ትኩረት ሰጥቷል።
የፓርቲው አባላት ከህዋስ ጀምሮ ባሉት ሁሉም ተቋማት ነፃ የሀሳብ ትግል እያደረጉ የዴሞክራሲን ባህል እየገነቡ ነው ፤ የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤን አስመልክቶ በየደረጃው በተካሄዱ የቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንሶችም ዴሞክራሲያዊነት ተንፀባርቋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በሁለተኛው ጉባኤ ዙርያ አጭር ኦረንቴሽን የሰጡ ሲሆን ፣ ከወረዳ መሠረታዊ ድርጅት እስከ ክ/ከተማ ድረስ እየተከናወነ ያለው የቅድመ ጉባኤኮንፈረንስም በነገው እለት በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ መድረክ የሚደረግ እንደሆነም ተመላክቷል!!
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.