ዛሬ ባለ 13 ወለል የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ባለ 13 ወለል የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ ግንባታን አጠናቅቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::

ዘመኑን የሚመጥን የስራ አካባቢ ለመፍጠር በተለያዩ አካባቢዎች ተበታትነዉ ሲሰጡ የነበሩትን አገልግሎቶች ን ወደ አንድ ማእከል በማሰባሰብ አገልግሎት የሚሳልጥ ፣ ለአካል ጉዳተኞችም ምቹ፣የአገልጋይ እና የተገልጋይ እንግልት የሚቀንስ፣ ስማርት ሲቲን የመፍጠር ግባችንን ለማሳካት የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ተካትተውበት የተገነባ ሲሆን በውስጡ 120 ቢሮዎችን ጨምሮ እያንዳንዳቸው 1500 እና 500 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሁለት የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ በቂ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ጂምናዚየም፣ የሕፃናት ማቆያና መጫወቻ ቦታ እና መሰል መገልገያዎች ተሟልተዉለታል።።

በተጨማሪ ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት በጥራት ገንብተን ያጠናቀቅነው ይህ ህንፃ ዉጪን በመቆጠብ ከዚህ በፊት ለቢሮ ኪራይ የምናውለውን ሀብት በማስቀረት ለልማት እንድናውል ያስችለናል::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.