የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 ዓ.ም 2ኛው ዙር ዕጩ የሠላም ሠራዊት አባላትን በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታድየም አስመረቀ።

በምረቃ መርሃግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ከህዝብ የተወጣጣና የከተማችን ዋነኛ የሰላም ዘብ የሆነው የሰላም ሰራዊታችንን አሰልጥኖ እንዲመረቅ ማደረግ ከፀጥታ አጠባበቅ ስራ ግን ለጎን በህዝቦች መካከል መቀራረብን፣በጋራ አጀንዳ ላይ መግባባትና የህዝቦችን ትስስር በመፍጠር አንድነትና ወንድማማችነትን ማጠናከር ዓላማው ያደረገ ተግባር ነው ብለዋል።

የከተማችን ስላምና ፀጥታ ለማስተዳደር ፣ የደንብ ጥሰቶችን ለመከላልና ለመቆጣጠር ከህዝብ የተወጣጡ ጠንካራ የሰላም ስራዊት አደረጃጀት በመፍጠር የህዝብ የሰላም ባለቤትነት ማጠናከር ተገቢ ነው ያሉት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ የዛሬው የፀጥታ አጋዥ ሃይል የንድፈ ሀሳብ እና ወታደራዊ ስልጠና ምረቃም አደረጃጀቱ በሰው ሀይል የማጠናከር ስራችን ማሳያ ሲሆን በዚህ የስልጠና ሂደት የሰላም ሰራዊት አባላት ጠንካራ የህግ አስከባሪ ሃይል እንዲሆን ይጠበቃል ብለዋል።

የዛሬው ተመራቂዎች በቀጣይም የፀጥታ አጠባበቅ ስራ ላይ የሚሰጣችሁን ኃላፊነት በተገቢው እንድትወጡ አደራ ጭምር እያሳሰብኩ ለዚህ ውጤትና ስልጠናው በወጣለት መርሀ ግብር እንዲጠናቀቅ ሌት ተቀን ጥረት ላደረጉ አመራሮች፣የፖሊስ ኃሊፊዎች፣አሰልጣኞች፣ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች፣በየደረጃው የፀጥታ አሰተዳደር ተቋማት አመራርና ባልደረቦችን አመስግነዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮምሽነር ጌቱ አርጋ በበኩላቸው በከተማችን አዲስ አበባ በ4 ዓመቱ የለውጥ አመታት ውስጥ ጠላቶቻችን ሁከት ለመፍጠር ያላደረጉት ጥረት የለም። ነገር ግን የፀጥታ መዋቅሩ፣የሰላም ሠራዊትና ሕብረተሰቡ ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ሊከሽፍ ችሏል። ለዚህም ሁሉንም ተቋማት አመስግናለሁ ብለዋል።

የዛሬ ተመራቂዎች መጪው የጥምቀት በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሠላም ተከብሮ እንዲያልፍ ከፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ አሳስባለሁ ብለዋል።

የቢሮ ም/ል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ በበኩላቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017ዓ.ም 11,000 ዕጩ አዲስ የሰላም ስራዊት አባላት ለተከታታይ 15 ቀናት በንድፈ ሐሳብ እና የመስክ ወታደራዊ፣ የአካላት ብቃት ወንጀልን መከላከል፣የስጋት ቦታው ልየታ እና አካላዊ ፍተሻ፣በዕውቀት በክህሎት በአመለካከት እና በአካላዊ ብቃት ዝግጁ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.