እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ!!
ጥምቀት በዓለም ካስተዋወቁን ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓሎቻችን አንዱ ነው። የኅብረ ብሔራዊነት መገለጫ የሆነው የጥምቀት በዓል ኢትዮዽያዊያን በባህላዊ አልባሳት ደምቀዉ በተለያዩ ቋንቋዎች ሀይማታዊ እና ባህላዊ ትዕይንቶችን የሚያሳዩበት የእኛነታችን መገለጫ በዓል ነው።
በርካታ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በዚህ በዓል ላይ የሚታየውን ሀይማኖታዊ ትዕይንት፣ ባህላችንን፣ ዉበታችንን፣ ድምቀታችንን፣ አብሮነታችንን እንዲሁም እሴቶቻችንን ተመልክተዉ ይደነቁበታል።
ጥምቀትን ስናከብር፤ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቱን በማጎልበት፣ ኅብረ ብሔራዊነቱን በማጠናከር፣ ለቱሪዝም ዘርፍ እድገት እና ለሀገር ገፅታ ግንባታ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ በማጉላት፣ ዉብ እና ደማቅ በሆነ ሁኔታ ሊሆን ይገባል።
በዓሉ አብሮነት ሚጎለብትበት፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የደስታ እንዲሆን የመልካም ምኞት መልእክቴን አስተላልፋለሁ።
መልካም የጥምቀት በዓል ይሁን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.