አገልግሎት አሰጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ በመ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አገልግሎት አሰጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ በመምጣቱ ተደስተናል፡-የአሜሪካ ኤምባሲ ተወካዮች

የ አዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ በመምጣቱ ተደስተናል ሲሉ የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ የጎበኙ የአሜሪካ ኤምባሲ ተወካዮች ገለጹ፡፡

ከአሜሪካ ኤምባሲ የተዉጣጡ አካላት የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ በማዕከል ፣ በቦሌ እና በቂርቆስ ቅርንጫፍ ተዘዋዉረዉ ተመልክተዋል፡፡

ባለሥልጣኑ የኮር ዲፕሎማት የተሽከርካሪና እና የአሽከርካሪ አገልግሎት ( የዉጭ መንጃ ፈቃድ ቅያሬ)፣ የእድሳትና ሌሎች አገልግሎቶችን ይሰጣል።

የሀገራትን የእርስ በርስ ትስስር ለማጠናከር የኮር ዲፕሎማት አገልግሎቶች የቪአይፒ መሶኮት ተዘጋጅቶ አገልግሎት የሚያገኙበት አሰራር መዘርጋቱ ተመልክቷል፡፡

የአሜሪካ ኤምባሲ በዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑት ተቀሟት ዉስጥ አንደኛዉ ነዉ::

ከአሜሪካ ኤምባሲ የተዉጣጡ አካላት የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ በማዕከል ፣ በቦሌ እና በቂርቆስ ቅርንጫፍ ተዘዋዉረዉ ተመልክተዉ ከቀደሞዉ ጋር በማነፃፀር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ በመምጣቱ መደሰታቸዉን ገልፀዋል ::

በተቋሙ በርካታ የአለም አቀፍ ድርጅቶች እና የ132 ኤምባሲዎች ንብረት የሆኑ ከ11ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ተመዝግበዉ የሚገኙ መሆኑ ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

AMN


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.