ዛሬ በመንግስት እና ግል አጋርነት መርሀ ግብር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በመንግስት እና ግል አጋርነት መርሀ ግብር ከአያት አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር የ13,752 ቤቶች ግንባታን አስጀምረናል::

በካዛንቺስ አካባቢ ከኦቪድ ግሩፕ ጋር ካስጀመርነው ጋር ከ15 ሺሕ በላይ ቤቶችን የምናለማ ሲሆን ቅድሚያ የማልማት መብታቸውን በመጠቀም የሚገነቡ የግል አልሚዎችን ጨምሮ በጠቅላላው 20 ሺሕ ቤቶችን የሚገነቡ ይሆናል::

በከተማችን ያረጁ እና ለመኖር ምቹ ያልሆኑ እንደ ካዛንቺስ ያሉ አካባቢዎችን መልሰን ስናለማ በዋነኛነት የህዝቡን ዋንኛ አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነውን የመኖሪያ ቤትን ለመመለስ ሲሆን የመኖሪያ ቤቶችን ስንሰራ ቤት ብቻ ሳይሆን ለኑሮ ምቹ የሆነ አካባቢዎችን እንገነባለን::

ካሳንችስ ከመልሶ ማልት በፊት ነባር 8000 መኖሪያና ንግድ ቤቶች በጥቅሉ ወደ 21ሺ ነዋሪዎችን የሚገለገሉበት አካባቢ የነበረ ሲሆን በመልሶ ማልማት ስራችን ሁለት ሺሕ የንግድ ሱቆች እና ሀያ ሺሕ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ከ100 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች የሚገለገሉበት አካባቢ ይሆናል።

ካዛንቺስ ላይ የምንገነባው ይህ የካዛንቺስ አያት መንደር በውስጡ ማህበራዊ ግልጋሎትን የሚሰጡ ተቋማት ጨምሮ የመማሪያ ቦታዎች፣ የጤና ተቋማት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ አረንጏዴ ቦታዎች፣ ሞሎች፣ ሱቆች እንዲሁም ሰፋፊ የመኪና ማቆሚያዎችን ያካተተ ግዙፍ ፕሮጀክት ሲሆን ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር ነው::

በሚቀጥሉት 18 ወራት ጊዜ ውስጥ የ15 ሺህ ቤቶች ግንባታን ለማጠናቀቅ ያቀድን ሲሆን ሁላችንም ለፕሮጀክቱ ስኬት በጋራ እንድንሰራ አደራ እያልኩ ንጹህ፣ ፅዱ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ተወዳዳሪ የሆነች አለም አቀፍ ከተማ መገንባታችንን አሁንም አጠናክረን ቀጥለናል::

ያስጀመረን ፈጣሪ በድል እንድናጠናቅቅ ይርዳን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.