በተፈጥሮ ሀብት በታደለችው ታሪካዊቷ ጅማ ከተማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በተፈጥሮ ሀብት በታደለችው ታሪካዊቷ ጅማ ከተማ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ስራ እና የታሪካዊዉን የአባጅፋር ቤተ መንግስት እድሳት ጐብኝተናል።

መንግስታችን የቅርሶችን እድሳት እና የኮሪደር ልማት ስራን በመዲናችን አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የሀገራችን ከተሞችም በመጀመር ከተሞቻችንን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እና ጽዱ እንዲሆኑ እንዲሁም የቱሪስት መስህብነታቸው እንዲጨምር በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

እንግዳ ተቀባይና ሰላም ወዳዱን የጅማ ከተማ እና የአካባቢውን ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ ወደር በማይገኝለት ተሳትፏቸሁ ይህ ራዕይ እውን እንዲሆን በማስቻላችሁ እና ላሳያችሁን ፍቅር ታላቅ ምስጋና ይገባቹሃል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.