ከህጻንነታቸዉ ጀምሮ በኮልፌ የወንዶች ልጆች ማሳደጊያ እና በቀጨኔ የሴቶች ማሳደጊያ ማዕከል ካሳደግናቸው ልጆቻችን መካከል ሰባቱን ለወግ ለማዕረግ አብቅተን የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ለመፈጸም ያበቃን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን:: ሙሽሮች እንኳን ደስ ያላችሁ!
እንኳን ፈጣሪ በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ረድቷችሁ ለዚህ ለተባረከ እና ለተቀደሰ የህይወታችሁ ምዕራፍ ቀን እንኳን አደረሳችሁ:: መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ!
የከተማ አስተዳደራችን ወላጅ ለሌላቸዉ ወላጅ እና ቤተሰብ በመሆን አሳድጎ፣ ለወግ ለማዕረግ እንዲበቁ ከማድረግ በተጨማሪ በቀጣይ የህይወታቸው ምዕራፍ የስራ እድል በመፍጠር ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ዉጤታማ ህይወት እንዲኖራቸው እየተመኘን በዚህ በተቀደሰ ስራ የተሳተፉትን ሁሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
በድጋሚ መልካም ጋብቻ
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.