"የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በኢትዮ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማምጣት ራዕይን ለማሳካት የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ ይጠበቃል" ክቡር አቶ አደም ፋራህ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት

ከጥር 23 አስከ 25 በሚካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማምጣት ራዕይን ለማሳካት የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤን በማስመልከት መግለጫ የሰጡት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጉባኤውን የተሳካ ለማድረግ አብይ እና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተደራጅተው ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን እና በአሁኑ ወቅትም ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

“ከቃል እስከ ባህል” የሚለው የጉባኤው መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ ተልዕኮን በአግባቡ የሚገልጽና ፓርቲው በጉባኤው፣ በፕሮግራሞቹ እና በምርጫ ወቅት የገባቸውን ቃሎች እና ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች በስኬት ተግባራዊ ማድረጉን እና የፓርቲውን ቀጣይ አቅጣጫ አመላካች መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ጉባኤው በሶስት ምክንያቶች ከፍተኛ ትኩረትን እንደሚስብ የገለጹት አቶ አደም ታላቅ ህዝብና ሀገርን የሚመራ ፓርቲ የሚያደርገው ጉባኤ መሆኑ አንዱ ትኩረት የሚስብበት ምክንያት ነው ብለዋል።

15 ነጥብ 7 ሚሊየን አባላት ያሉት ከአለማችን ግዙፍ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው እና በሁሉም መስኮች ስኬቶችን እያስመዘገበ የመጣው ብልጽግና ፓርቲ የሚያካሂደው ጉባኤ መሆኑ በራሱ ትኩረት እንዲሰጠው ያደርገዋል ብለዋል አቶ አደም።

በጉባኤው ፓርቲውን እና መንግስትን የሚያጠናክሩ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተቀመጠውን የፓርቲውን ራዕይ እውን ማድረግ የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይወሰናሉ ያሉት አቶ አደም ቀጣይ አቅጣጫዎችም ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል፡፡

በጉባኤው 1ሺ 700 በድምጽ የሚሳተፉ እንዲሁም ያለ ድምጽ የሚሳተፉ የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች እና የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች እንደሚሳተፉም ተገልጿል።

15 የሚደርሱ ከተለያዩ የአለም ሀገራት የእህት ፓርቲ ተወካዮችም በጉባኤው በመሳተፍ አጋርነታቸውን ያሳያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል።

prosperity


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.