.png)
ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ የሲሚንቶ ኢንደስትሪ ለኃይል ግብዓት ፍላጎቱ ከውጭ ሀገራት በሚገባ የድንጋይ ከሰል ምርት ላይ ተመርኩዞ ቆይቷል።
ይሁንና ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል ለመጠቀም በመንግሥት በተደረገ ድጋፍ ትርጉም ያለው ለውጥ ተገኝቷል። በዚህ የተነሳ ከውጭ በሚገባ የድንጋይ ከሰል ላይ የነበረው የ100% ተፅዕኖ ወደ 34.15% ዝቅ ብሏል።
የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል የመጠቀም ምጣኔም ከ0% ወደ 65.85% እመርታ አሳይቷል። ይኽ ለውጥ ከውጭ ከሚገቡ ይልቅ የሀገር ውስጥ ኃብት ቅድሚያ ሰጥቶ የመጠቀም ፖሊሲን ውጤታማነት የሚያሳይ ሲሆን የኃይል ምንጭ ማረጋገጥ እና በውጭ ኃብት ላይ መመርኮዝንም ይቀንሳል።
በዚህ ለውጥ አንዱ ቁልፍ ባለሚና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በዳውሮ ዞን በተርጫ አካባቢ ክሌሌ ላይ ያለው ኢቲ ሚኒራልስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ፋብሪካ ነው። ይኽ ፋብሪካ በሰዓት 150 ቶን በማምረት እያደገ ለመጣው ፍላጎት ለሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል ምርት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረክታል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.