.png)
"የከተማዋን ሁለንተናዊ ስራዎችን በመልዕክትና በአጀንዳ በመምራት የመጡ ተጨባጭ ለዉጦችን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በ 6 ወራት ያከናወናቸዉን ቅንጅታዊ እና መደበኛ ስራዎችን አፈፃፀም ገመገመ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በ 6 ወራት ያከናወናቸዉን ቅንጅታዊ እና መደበኛ ስራ አፈፃፀሙን የቢሮዉ አመራሮችና ሰራተኞች፤የሴክተር ተቋማትና የክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊዎች እና የሴክተር ክላስተር አስተባባሪዎች በተገኙበት ገምግሟል፡፡
የቢሮዉ ፅ/ቤት ኃለፊ ወ/ሮ ነፃነት አለሙ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ጊዜ ዉስጥ እቅድን የጋራ በማድረግ ተግባብቶ በፍጥነት ወደ ተግባር በመግባት በየደረጃዉ ካሉ መዋቅሮች ጋር በሁሉም የከተማዋ አጀንዳዎች ላይ ግንባር ቀደም ሆነን በቅንጅት በመስራታችን የተሻለ ዉጤት ማምጣት ችለናል ብለዋል፡፡
ኃላፊዋ አክለዉም በከተማችን የሚታየዉን ፈጣን እድገት የሚመጥን ወቅታዊ፤ ፈጣንና ጥራት ያለዉ መረጃን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለዉን መዋቅራችንን በሁለተናዊ መልኩ በማዘመን እና ስታንዳርዱን በማሳደግ ተወዳዳሪ ተቋም ለመፍጠር በምናደርገዉ ጥረት በጋራ የበለጠ አበክረን እንሰራለንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ቢሮዉ በበጀት ዓመቱ በቅንጅታዊ አሰራር የተሻለ አፈፃፀም ላመጡ ተቋማት የእዉቅና ምስክር ወረቀት ሽልማት አበረክቶላቸዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.