
የአዲስ አበባ ዕድገት ከሀገር አልፎ አህጉራዊ ፋይዳ ያለው ነው -ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ
አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ የከተማዋ ዕድገት ከሀገር አልፎ አህጉራዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት 2ኛውን የብልፅግና መደበኛ ጉባኤ በማስመልከት ባለፉት የለውጥ አመታት በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡
ከተማዋ ደረጃዋን የጠበቀች እና አለም አቀፍ ስብሰባዎችን ማስተናገድ በሚያስችል መልኩ የተለያዩ አገልግሎት መስጫዎች ያሏት መሆኗን ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡
መዲናዋ በአፍሪካ ሕብረት እና በተለያዩ አህጉራዊ መድረኮች ላይ ለመታደም ለሚመጡ እንግዶች የአፍሪካ መዲናነቷን መልክ የሚገልጽ የልማት ስራዎችን ማከናወኗን መመልከታቸውን ጠቁመዋል፡፡
ይህ መዲናዋን የማስዋብ መልካም ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.