"የህብረት ስራ ማህበራትን ሀብትና ንብረት ከብክ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የህብረት ስራ ማህበራትን ሀብትና ንብረት ከብክነት በመጠበቅ የአባላትና የህብረተሰብ ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን!"

ዓላማውን  የሕብረት ስራ ማህበራትን ሪፎርም በማድረግ እና በየደረጃው የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራትን አቅም በማጎልበት የሚስተዋሉ የብልሹ አሰራር ችግሮችን በማረም ለአባላቱና ለከተማው ነዋሪ የተሻለ አገልግሎት መስጠት መሰረት ያደረገ የውይይት መድረክ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ተካሂዷል።

"የህብረት ስራ ማህበራትን ሀብትና ንብረት ከብክነት በመጠበቅ የአባላትና የህብረተሰብ ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል በተካሄዱት በነዚህ መድረኮች ተቋሙን በአሰራር፣ በአደረጃጀት፣ በሰው ሀይል  እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሪፎርም በማድረግ ተቋማቱ  የተሻለ ስራ እንዲሰሩ ለማስቻል ሲሆን የህብረት ስራ ማህበራቱ የሚፈለገው ለውጥ እንዲመጣ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ ተጠቅሷል።

የህብረት ስራ ማህበራት የዋጋ ማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን ከማቃለል አንፃር ሚናቸው እጅግ የጎላ በመሆኑ ይህንኑ አጠናክሮ ለመቀጠል እና የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም የህብረተሰቡንና  የአባላቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ማሕበራቱን እንደ አስፈላጊነቱ ሪፎርም እያደረጉ  መስራት እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በውይይት መድረኮቹ በየደረጃው የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት ማህበራት አመራሮች፣ አባላት፣ ስራ አመራር ቦርድ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.