የኢትዮጵያ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኢትዮጵያ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ክብር እና ጥቅም ላይ በመተባባር በመከባበር ይሰራል፡- የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ

የኢትዮጵያ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ክብር እና ጥቅም ላይ በመተባባር እና በመከባበር እንደሚሰራ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ገለጹ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባኤው ላይ መልእክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ፣ የምክር ቤቱ አባል የፖለቲካ ፓርቲዎች ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የሚያደርገትን ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ ፉክክር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል፡፡ 

ምክር ቤቱ በአገሪቱ ክብር እና ጥቅም ላይ በመተባባር እና በመከባበር በመስራት የሰለጠነ የፖለቲካ ልምምድ ለማዳበር ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ዋስትና ያለው እውነተኛ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዲዳብር ፣ዲሞክራሲ እውን እንዲሆን ፣  ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም ልማት እንዲረጋገጥ ከፍተኛ ሚና አላቸውም ብለዋል፡፡

አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በአገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ.ም የቃልኪዳን ሰነድ ተፈራርመው የጋራ ምክርቤት ማቋቋማቸውንም አውስተዋል፡፡

ይህም በአገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዲጎለብት አዲስ ምእራፍ ሆኖ ተመዝግቧል ብለዋል፡፡ 

በ2010 ዓ.ም የተካሄደውን ሪፎርም ተከትሎ የተጀመረው የፖለቲካ ሽግግር እንዲሳካ የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርሻቸውን መወጣታቸውንም አስረድተዋል፡፡  

በአገራችን ተንሰራፍቶ የቆየውን የመጠፋፋት የፖለቲካ ባህል በመቀየር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ መተባበር፣ መተራራም እና መፎካከር የሚያስችል የፖለቲካ ምህዳርን ለማስፈን የጋራ ምክር ቤቱ የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያደርግ መቆየቱንም ተናግረዋል፡፡ 

ምክር ቤቱ ሲመሰረት  በአገሪቱ ፋና ወጊ ሆኖ ብቅ ማለቱን ያወሱት ሰብሳቢው፣ የምክር ቤቱ አባል የፖለቲካ ፓርቲዎች ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ባሳዩት ቁርጠኝነት ዛሬ ምክር ቤቱ እስከ ወረዳ እንዲዋቀር ተደርጓል ብለዋል፡፡


በበዚህም የሰላም እና የዲሞክራሲ ልምምድ መድረክ ሆኖ እያገለገለ መሆኑን አውስተዋል፡፡ 


ብልጽግና ከምክር ቤቱ አባልነት ባሻገር አስቻይ ሁኔታን በመፍጠር ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር  በወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እንዲደረግ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን አውስተዋል፡፡ 


ብልጽግና በአገሪቱ አዲስ የዲሞክራሲ ባህል እንዲዳብር እያደረገ ላለው አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ 


ምክር ቤቱ ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በጋራ  በመስራት  የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡  


ጉባኤው የተሳካ እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.