የትግራይን ህዝብ ወደ ዳግም ጦርነት ለማስገባት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የትግራይን ህዝብ ወደ ዳግም ጦርነት ለማስገባት የሚሞክሩ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጠየቁ

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሰላም መሆኑን የሚያሳይ ሰልፍ ከማለዳ ጀመረው እያካሄዱ ነው።

በሰልፋቸውም የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሰላም በመሆኑ የትግራይን ህዝብ ወደ ዳግም ጦርነት ለማስገባት የሚሞክሩ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።

ፖለቲከኞች እና የትግራይ ልሂቃን በውስጣቸው ያለውን ልዩነት በመግባባትና በመነጋገር ብቻ እንዲፈቱ የጠየቁት ሰልፈኞቹ የትግራይን መሬት የጦርነት ምድር ለማድረግ የሚሞክሩ ሃይሎችን በጋራ መታገል እንደሚገባም አሳስበዋል።

የትግራይ ህዝብ ከትላንት የጦርነት ሰቆቃ ያልወጣ በመሆኑ "ልማት እንጂ ጦርነትን የሚሸከምበት አቅም የለውም" በማለትም ሰልፈኞቹ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

የትግራይ የፖለቲካ ሀይሎች የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት እንዲያከብሩና ለሰላም ዝግጁ እንዲሆኑም በሰልፉ ላይ ተነስቷል።

AMN


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.