
"የዓድዋ ድል መታሰቢያ ትውልዱ የተዛባ ታሪኩን ያቀናበት ብቻ ሳይሆን አሁን ለጀመርነው ሃገራዊ ምክክር ጉልበትና አቅም መፍጠር የሚችል ነዉ" ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ
ዛሬዉ እለት ከመላዉ ሃገሪቱ የተውጣጡ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዉያን ቤተክርስቲያን ካዉንሲል መካነእየሱስ ፕሬዘዳንትና የካዉንሲሉ ስራ አስፈፃሚ አባል ቄስ፤ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ የአንድነት ፓርክንና የአድዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸዉን ጠቅሰዉ ሁለቱም ታሪካዊ ስራዎች የሀገርን ገፅታ ከማጉላታቸዉ በላይ ትዉልዱ በሃገሩ እንዲኮራና የድርሻዉን እንዲወጣ አደራ የሰጠ ነዉ ብለዋል።
ፕሬዚደንቱ አክለዉም፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ትዉልዱ የተዛባ ታሪኩን ያቀናበት ብቻ ሳይሆን ምስክርነት የተገለጠበት አሁን ለጀመርነዉ ሃገራዊ ምክክር ጉልበትና አቅም መፍጠር የሚችል ነውም ብለዋል።
በመጨረሻም ጎብኚዎቹ የሀገር በጎ ገፅታን ማስቀጠልና ለሃገር አንድነት መቆም ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ገልፀው አንድነት ካለን ያለንን በመጠቀም የሌለንን ማምጣትም እንችላለን ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.