የተከታታይ የምስል አቅርቦቱን ምንጀምረው በአዲስ አበባ ከተማ ነው። በሁለተኛው ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ምን እየተከናወነ ነው?
ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ በአዲስ አበባ በ8 አካባቢዎች እየተከናወነ ነው።
በሁለተኛው ምዕራፍ የሚከናወነው የኮሪደር ልማት በአጠቃላይ 2 ሺህ 879 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን፤ 240 ኪሎ ሜትር የአስፋልት እንዲሁም 237 ኪሎሜትር እግረኛ መንገድ በመገንባት ላይ ነው።
በስምንቱም የኮሪደር ልማት ስፍራዎች 32 የህጻናት መጫዎቻ ፤79 የሚሆኑ ህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች እንዲሁም 114 የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግና የታክሲና አውቶብስ ተርሚናሎችን ያካተተ መሰረተ ልማት ይከናወናል።
ከትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች መካከል 58 በሚሆኑ አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ጣቢያዎች ይኖራሉ።
ከ100 ኪሎሜትር በላይ የሚሆን የብስክሌት መንገድም በመገንባት ላይ ነው።
የከተማዋ ነዋሪዎች ጤናቸውን የሚጠብቁባቸው 17 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችም ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋሉ።
በኮሪደር ልማት ስራው ከእንጦጦ -ቀበና-ግንፍሌ ፒኮክ እንዲሁም ከእንጦጦ-ወዳጅነት-ፒኮክ የሚደርሱ ሁለት የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎችም እየተከናወኑ ነው።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.