
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ተኛ አመት 7ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
1ኛ .በከተማዉ አስተዳደር በጀት ተመድቦላቸዉ የተገነቡ እና በመጠናቀቅ ላይ ያሉትን አዳዲስ ሆስፒታሎችን ዘመኑን በዋጀ የህክምና መሳሪያ ለማሟላት እና አለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟላ አገልግሎት መስጠት ያስችላቸው ዘንድ በዘርፉ ትልቅ ልምድ ካካበቱ የግል ሴክተር ጋር በአጋርነት ለመስራት ዉሳኔ አሳልፏል።
2ተኛ .አንዳንድ የመንግስት አገልግሎቶችን በውል ለ3ተኛ ወገን ለማስራት የወጣውን ረቂቅ ደንብ መርምሮ በማየት ካቢኔዉ አፅድቋል።
3ተኛ .የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ላላቸው እና ተኪ ምርቶችን ለሚያመርቱ ኢንዲስትሪዎች ባቀረቡት የማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎች ላይ በጥልቅ በመወያየት እና የአተገባበር አቅጣጫ በማስቀመጥ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
4ተኛ .የኮሪደር ልማት ውጤት ከሆኑት ሥራዎች አንዱ የብዙሀን ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ችግሮች የሚያቃልል እና የትራፊክ ፍስቱን የሚያሻሽለው የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብን በመመርመር አፅድቋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.