ዛሬ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸማችንን መገምገ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸማችንን መገምገም ጀምረናል።

ባለፉት ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸማችን ከተማችንን ከነዋሪዎቿ ኑሮ እና አኗኗር ጋር አስተሳስረን ውብ እና አበባ የማድረግ እንዲሁም የቱሪስት መተላለፊያ ሳትሆን መዳረሻ እንድትሆን ለማድረግ አቅደን እየሰራን ያለነውን ስራ ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ማድረግ  እና ውጤታማነቱን ማስጠበቅ ችለናል።

አስተዳደራዊ ወጪን እና ብክነትን በመቀነስ ከህዝብ ከሰበሰብነው ግብር 70 % የሚሆነውን የነዋሪዎቻችንን እንግልት ለሚቀንሱ እና ህዝብን ለሚጠቅሙ ተግባራት እንዲሁም ለዘላቂ ልማት በማዋላችን የፈጣን ለዉጦቻችንን ቀጣይነት አስጠብቀናል።

አገልግሎት አሰጣጣችንን ቀልጣፋና ከብልሹ አሰራር የጸዳ ለማድረግ እና መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት አሰራራችንን ዲጂታላይዝ ለማድረግ አቅደን የሰራናቸው ስራዎችም ለውጦችን አሳይተዋል።

የግምገማ መድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸማችን ባስመዘገብናቸው ስኬቶች ሳንረካ አቅደን ያልፈፀምናቸዉን እና  ድክመቶቻችንን ከነመንስዔዎቻቸው ለይተን በመገምገም ለቀጣይ ውጤታማነት የምንዘጋጅበት  ይሆናል።
  
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.