ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኮማንዶ እና አየር ወለድ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኮማንዶ እና አየር ወለድ እዝ የሰራዊት አመራሮችን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተቀብለው አነጋግረዋል::

ከሻለቃ በላይ ያሉ የሰራዊት አመራሮቹ በጉብኝቱ መደሰታቸውን የገለጹ ሲሆን የኮማንዶ እና አየር ወለድ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታ በበኩላቸው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ምንም አይነት ልዩነት ቢኖር በሀገር ጉዳይ በጋራ በመቆም ፈተናዎችን የማለፍ ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው የኮማንዶ እና አየር ወለድ እዝ የሰራዊት አመራሮች እና ሰራዊቱ ለሀገር እየከፈሉት ላለው ውድ ዋጋ ምስጋናቸውን አቅርበው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለሀገር ውለታ የዋሉ ጀግኖች ቋሚ መታሰቢያ መሆኑንም ገልጸዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.